አስደሳች ዜና የመጽ xSdúC z@ ym{'F QÇS _ÂT bb@T WS_ l¸drg# _ÂèC y¸rÇ UÃq&ãCN õTLÝÝ

Unfortunately navigation hasn't been translated yet.

 

Note: If you do not see text properly, from the View menu of your browser click Encoding and then select Unicode (UTF-8)

 

አስደሳች ዜና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በቤት ውስጥ ለሚደረጉ ጥናቶች የሚረዱ ጥያቄዎችን ያካትታል፡፡

 

መግቢያ

 

እየሱስን የምንመሰክርላቸው ሰዎች በአካባቢያችን እንደሚኖሩ አያጠራጥርም። ለዚህ ዓላማ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ደግሞ እዚህ ተዘጋጅተዋል። እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ቤትዎ ይጋብዙና የምስራቹን ቃል አብራችሁ አጥኑ! እንዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥያቄዎች የተዘጋጁት በጃፓን በቤት ውስጥ ለሚደረጉ ጥናቶች ነው። ከተሳታፊዎች አብዛኛዎቹ የቡድሃ እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ናቸው። እንዚህ ጥያቄዎች በተለያዪ ሐገሮች በሚኖሩ ፕሮቴስታንቶች ተሞክረዋል። የአስደሳች ዜናዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥያቄዎችን ከተጠቀምን ምንም እንኩዋን የጥናቱ ተሳታፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ባይኖራቸውም ቡድኑን ለመምራት አስቸጋሪ አይሆንብንም።

 

መርሆዎች

 

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መሪ መስበክ የለበትም። እርሱ ጥያቄውን ሲያንብ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የአጥኒዎችን አእምሮ እንደሚከፍት ማመን አለበት።

 

አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከአንድ ሰዓት የበለጠ ጊዜ መውሰድ የለበትም። ቢበዛ አንድ ሰዓት ከሩብ መሆን አለበት። በሰዓቱ ጀምረን በሰዓቱ መጨረስ አለብን። ይህንን ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። አለበለዚያ ስራ የሚበዛባቸው ሰዎች ሌላ ጊዜ መምጣት ያቆማሉ።

 

 

 

 

© 2005 Glad Tidings Mission